Monday, April 1, 2013

ሳውዲ አረቢያ በዘመቻው የሚፈናቀሉት ዜጎች አሳሳቢነትና የእኛ ምልጃ.

ይህንን ጽሁፍ የወሰድኩት ነብዩ ሲራክ ከጻፈው የማለዳ ወግ ከሚለው ጽሁፍ ላይ ነው እና አዎ ይህ የሁላችንም ምልጃ ”ልመና ” ነው እባካችሁ ስሙን ለቦንድ እና ለተለያዩ ነገሮች ስትሰበስቡን እንደምንሰማችሁ እናንተም ዛሬ ስሙን በሳኡድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ድምጽ…………..
በዘመቻው የሚፈናቀሉት ዜጎች     http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/04/01/65476/

እኔም እንዳቅሜ ሚጢጢዬ ትዝታ ፑሽኪን ውስጥ አለኝ፡



ወዳጄ አደም ሁሴንን የፑሽኪን ትዝታህ ሳየው ምላሽ ልሰጥ ግድ አለኝ፡፡ እኔም እንዳቅሜ ሚጢጢዬ ትዝታ ፑሽኪን ውስጥ አለኝ፡፡ ጋሽ አያልነህን በብዙ ነገር አድናቂው ብሎም አክባሪው ነኝ፡፡ ብዙ አማተር ገጣሚያን ያጡትን መድረክ አዘጋጅቶ እንኩ ያለ…ለጥበብ ስለጥበብ ብዙ የደከመ ነው፡፡ በተለይ ተተኪ ተዋንያን እና ገጣሚያን የማውጣቱን ነገር የእሱን ያህል የሰራ፣ የደከመ አላየሁም፡፡ ይህንን ስል የጋሽ ተስፋዬ አበበን ውለታ ረስቼ አይደለም፡፡ ጋሽ ተስፋዬ(ፋዘር) ራሱን የቻለ ቦታ ያስፈልገዋል፡፡
   አንቱ የተባሉትም ለወጣቶች እውቀታቸውን እንዲያካፍሉ እና እነሱም እንዲከበሩ ለማድረግ ወርሃዊ የግጥም ምሽት  ማዘጋጀቱ በልቤ ውስጥ ቦታ እንድሰጠው ያደረገኝ ነገር ነው፡፡ ስንቶችንስ ለቁም ነገር አድርሷል? ስንቶች ከትላልቆች ትምህርት እንዲቀበሉ አድርጓል? እናንተው መልሱት፡፡ እኔ ጽሁፌን ሳሳየው አንተ ጸሀፊ የመሆን ተስፋ የለህም ያለኝ ታዋቂ ደራሲን ሳስታውሰው ያናድደኛል፡፡ እሱን ለማግኘት የደከምኩበትን ጊዜም ሳስብ ያበሳጨኛል፡፡ በእርግጥ እሱ በሰጠኝ አስተያየት ተስፋ አልቆረጥኩም፡፡ ይባስ ጠነከርኩኝ፣ እልህ ተጋባሁኝ፡፡ እነዚህ አይነት አማተርን የሚያጫጩ ባሉበት ቦታ ጋሽ አያልነህን ማየት ምንኛ መታደል ነው፡፡
አደም ሁሴን ‹‹..አርቲስት ጥላሁን ገሰሰም አንድ የጋሽ አያልነህን ቲያትር ይሰራል እየተባለ በምን ምክንያት እንደቀረ አላውቅም ወይም ስራ እንዴ…? …… ብቻ ግን ያስቆጫል አንድ ቲያትር ተውኖ ቢሆን ኖሮ እንዴት ደስ ይል ነበር…….!›› ብለህ ነበር በዝክረ-ጽሁፍህ አዎ! ተብሎ ነበር፡፡ ግን አልሰራም፡፡
አንደኛ ጋሽ አያልነህ ካለበት ተደራራቢ ስራ አንጻር በወቅቱ ቶሎ ጽፎ መስራት አልቻለም፡፡ ሁለተኛ ጥላሁንም በተለያየ ወቅት ለስራ፣ ለህክምናም በተደጋጋሚ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር፡፡ በኋላም እግሩ ላይ ችግር ከመድረሱ ጋር ተከትሎ ነገሮች አልተገናኝቶም እንደሚሉት ሆኑ፡፡ ‹‹..ግን ያስቆጫል አንድ ቴያትር ተውኖ ቢሆን እንዴት ደስ ይል ነበር..››ላልከው ሁለት ቴያትሮች ሰርቷል፡፡
በ1946 እና በ1947 ሀገር ማህበር በነበረበት ጊዜ ‹‹መንገደ ሰማይ›› እና የሁለተኛውን ርዕስ በደንብ ባላስታውሰውም ‹‹የተኮነነች ነፍስ›› ይመስለኛል፡፡ ሁለቱም ላይ በብቃት የተውኖ እንደነበር የሞያ ጓደኞቹ 60ኛ አመቱን በሀገር ፍቅር ባከበረበት ወቅት ገልጸዋል፡፡