Sunday, June 2, 2013

ወደ ስደት ፍለጋ የወጣነው ያጣነውን ነገር ነው፡፡

ፍለጋ የወጣነው ያጣነውን ነገር ነው፡፡ወደ ስደት፡፡ ስደት ደግሞ አይደለም በባህርና በየብስ ቀርቶ ብዙ ምቾት ባለውና እስከ አሁንም ተወዳዳሪ ባልተገኘለት አይሮፕላን እንኳን ቢሆን ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳ የስደትን ገፅታ የሚቀይር አይደለም፡፡

የስደት ጓደኛ ለመሆን ምክንያት የሚሆኑን ነገሮች የተለየዩ ቢሆኑም የሁሉም ምክንያት ስደተኞች ስደተኛ የሚለውን ስም ያለ ምንም ክፍያ ይሸለማሉ፡፡

እኛ ኢትዮጵያዊ ነን በፍቅር፣በመተሳሰብና በመከባበር የሚያምን የተለየ ህሊና ያለን፡፡ ቋንቋ፣ባህልና ከለር ለያይቶ የፈጠረን አምላክ ኢትዮጵያን ስለሚወዳት ከሌሎች ሀገራት ለየት ሊያደርጋት ብሎ ነው፡፡አምላክ የ80 ምናምን ቋንቋና ባህል ባለቤት ቢያደርገንም መከበበርና መፋቀር እንዳለ ነው፡፡ እንደውም ሁሉም ብሄር በቋንቋው በባህሉ ለሌላው ክብር ሲሰጥ የተለየ ውበት እንዲኖረው ያርገዋል፡፡ እኛ የምናምረው በደስታ ብቻ አይደለም በሀዘንም እንኳን የሚያምር ውበት ያለን ህዝቦች ነን፡፡

አብሮ መብላት መጠጣት ጎርብትና ቡና መጠራራትም ያለው ከኛው የፍቅር ሀገሯ ኢትዮጵያ ነው፡፡ፈረንጅማ መች ይሄንን አድርጎት፡፡እንግዳ ተቀምጦ የሚፈልገው በሚበቃው መጠን እንግዳውን አስቀመጦ አቅርቦ ይበላል ይጠጣል፡፡ አንተ ብትሆን ግን ይህንን አታደርግም፡፡ ምክንያቱም የፍቅርና አብሮ በመብላት ከምታምነዋ ሀገር ኢትዮጵያዊ ስለሆንክ፡፡ ከቻልክ ያለችህን ተካፍላለህ ካልቻልክ ደግሞ አንተም ተርበህ ወደ ምትሄድበት ትሄዳለህ አልያም ረሃብ ሆድህን እያለወሰው ትቀመጣለህ፡እንጂ መች ትሞክረዋለህ፡፡ ልሞክረውም ብትል ያንቅሃል፡፡

ታድያ እንዲህ በሚያምር ውበት ካለው ህብረተሰብ ውስጥ የወጣን ከሆነ ስደት ላይ ምን አረመኔነትን አላበሰን፡፡

ዛሬ ስደት ወዳጃችን በሆነበት ዘመን ፈረንጅና አረብ እንደ እቃ እየቆጠረን ስንኖር እኛ ስለነርሱ የነበረንን ክብር አስብና ከልቤ እናደዳለሁ፡፡ ትላንት ምንም በማያውቀው ልጅ አዕምሮችን እንኳን ፀጉረ ለውጥ ስናይ አልያም በአከባቢያችን ሲያልፍ ካየን ፈረንጅ…ፈረንጅ…ፈረንጅ እያልን በዜማና በጭብጨባ ግማሽ መንገዱን ብቻው እዳይሆን እንሸኘዋለን ይህን ያህል ነው ከራሳችን መከበበርና መፈቃቀር አልፈን ዛሬ እንደ ሰው ለማይቆጥሩን ሰዎች እንኳን ያለን አክብሮት፡፡ ይህንን የወረስነው ከእናት አባቶቻችን ነው፡፡ይህ ማለት ደግሞ እነርሱም እንደ ልጅነት ፈረንጅ …..ፈረንጅ እያሉ በጭብጨባ ባይሸኟቸውም መንገድ እየለቀቁ በዓይናቸው መሸኘታቸው እንዳለ ነው፡፡

ይህን ግን ዛሬ ለራሳችን ወገን መሆን አቅቶናል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ስደት ኢትዮጵያዊነትን አስክዶናል ማለት ነው፡፡ካልሆነማ በመከራ ከሞት እየታገለ ለገንዘብና ለስሜት ተገዢ ሆነን በወገኖቻችን መከራ ባልተደሰትን፡፡ በአንድነት በመከባበርና በፍቅር የሚያምነው ሀበሻነታችን በዘር በሃይማኖት በቋንቋ ተከፋፍለን አንድነታችንን አፍረክርከን እርስ በራሳችን ባልተበላላን፡፡

አሁን አሁን አረቡ እንኳን ስራ ለመቀጠር ስንሄድ ሀበሻ ነሽ ወይስ ኦሮሞ እያሉ አንድ ያለመሆናችንን ስግሩን መስማት እንዴት ያማል አማራ ትግሬ ኦሮሞ ጉራጌ እያልን ብሄርና ቋንቋን እንደ ዜግነት ቆጥረን እራሳችንን ወገንተኛ አድርገን ኢትዮጵያዊታቸንን ውበት አሳጣነው፡፡ የሚገርመው አማራውም ብዙ ቅርንጫፎችን አውጥቶ ኦሮሞም የወለጋ የሰላሌ ..የላኛው የታችኛው እየተባለ በመንገድ እንኳን አብሮ ላለመሄድ ተጠያይፎ በስደት አማራው በኦሮሞው መከራ ኦሮሞው በትግሬው መከራ ……እየተደሰተ ለገንዘብ ወገን ወገኑን ቆሞ እየሸጠና እየገደለ የስደትን አስከፊነት ከዐረቡ ይልቅ የኛው ወገን አባሰብን፡፡ እግዚአብሄር በባረከው ኢትዮጵያዊ ደማችን ከውስጣችን ቀድተን ለመድፋት ምን አስፈለገን ፡፡

ስደትን አይደለም በመከፋፈልና በመለያየት በመተባበርና በመፈቃቀር ክንድ እንኳን ማሸነፍ አልተቻለም ፡፡ አሁን ኢትዮጵያዊነታችን ውበቱን አቷል ቋንቋን የሰጠን አምላክ ነው፡፡ እንደ መልካችን የፈጠረንም አምላክ ነው፡፡ ታድያ ከአንድ አፈር ተሰርተን ከአንድ ማህፀን ከኢትዮጵያ ወጥተን አንድ መሆን ለምን አቃተን፡፡ ቢያንስ

ከመከራው ሀገር ከስደቱ እያለን እንኳን እንድ ሆነን ጠላታችንን ስደትን እናሳዝነው ፡፡ እግዚአብሄር አምላክ ለሁላችንም ልቦናን ይስጠን፡፡