Wednesday, April 24, 2013

ጠ/ሚ ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ከጉማሬ ጋር ያመሳሰላቸው ሁለት ነገር

ጠ/ሚ ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ከጉማሬ ጋር ያመሳሰላቸው ሁለት ነገር
   ቀባጠሩ ‹‹…ግመሎቹም ይሄዳሉ ውሾች ይጮሀሉ…››
ግሩም ተ/ሀይማኖት
      ሰውዬው ሲታዩ ራሳቸው ተረት ይመስላሉ ግን የቀድሞው ጠ/ሚ ሲተርቱ እና ሲሳቅላቸው ወይ ሲሳቅባቸው አይተው መተረት ደጋግመዋል፡፡አልሳቅንላቸውም አልሳቅንባቸውም አልቻሉበትም፡፡ ተናገር ተብለው የተላኩንት ለመናገር ፓርላማ ብቅ ብለው ነበር ዛሬ፡፡ ታዘው ከተናገሩት ሁሉ ያስገረመኝ አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሁማንራይትን በተመለከተ የተናገሩት ነው፡፡
   ‹‹..ሁማንራይትን በተመለከተ የቀረበ ጥያቄ አለ፡፡ የእነሱ ጉዳይ ግመሎቹ ይሄዳሉ ውሾቹ ይጮሀሉ..ነው፡፡…›› አሉ፡፡ የሰዎች መብት አልተከበረም ብሎ የሚጠይቅ ውሻ ሆኖ ለሆዱ ህሊናውን ሸጦ እንደ እቃ በሪሞት የሚዘወር እንደሳቸው አይነት ሲንቦል ምን ሊባል ነው አልኩና አሰብኩ፡፡ ታዲያ ማሰብ ነው እንጂ በምንም መሰዬ ትንፍሽ አላልኩም፡፡ አፈር ስሆን እንደሳቸው አይነትማ ጉማሬ ይባላል እንዳይሉኝ፡፡ ምክንያቱም በሁለት ነገር ስለሚመሳሰሉ እውነት ነው ታስብሉኛላችሁ፡፡ በመልክ ከመመሳሰል አልፎ ሌላም የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፡፡ ታዲያ በአፍ በልቶ በአፍ መጸዳዳት ነው የሚያመሳስላቸው አላልኩም ልብ በሉ፡፡ እንደዛም ካልኩ ምኑ ነው ስህተት? ፓርላማ ውስጥ እንደዚህ ጭቃ ጅራፋቸውን ሲያወርዱት በአፍ ከመጸዳዳት በምን ይተናነሳል፡፡ ከጉማሬውስ በምን ተለይተዋል ማለት እችል ነበር፡፡ ‹‹…እዚህ ህዝብ ሲበጠብጥ ቆይቶ…›› ብለው ከሳቸው የማይጠበቅ ቃላት ተፉ፡፡ ለነገሩ ረስቼው ነው ከሳቸው የማይጠበቅ ያልኩት መቼ የራሳቸውን አውርተው ያውቃሉ፡፡
  ከቀረበላቸው ኩንታል ጥያቄ ውስጥ የአማራው ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መፈናቀል አስመልክተው የቤንሻንጉል ባለስልጣናት ላይ ለጎዱላቸው፡፡ አጥረገረጉዋቸው፡፡ ያኙኛው እንዲህ በጎለደፈ አንደበት አልነበረም የሚለጉዱት፡፡ቢያንስ በዙሪያቸው ያሉ እንዲያጨበጭቡ አለያም እንዲያገጡ ያደርጉ ነበር፡፡ ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ ማለት ይሄኔ ነው፡፡ ለመሳደብ እንኳን የሚጠቀሙበት ቃላት በጣም የወረደ ነው፡፡ እነዚህን ባለስልጣናት ከነድንቁርናቸው፣ ከነሌብነታቸው አንስቶ ስልጣን ላይ ቂብ ያደረጋቸው እሳቸውን ከአፈር አንስቶ ተናጋሪ ጉቶ ያደረጋቸው ገዢ መንግስት መሆኑን ረሱት እንዴ? ትንሽ ከረም ስላለ ረስተውት ካልሆነ እሳቸውም ከደቡብ ክልል እንዴት እንደተባረሩ ያውቃሉ እኮ፡፡ አለቆቻቸው አላማቸውን ለማስፈጸም ያዘዙዋቸውን ሰርተው ሲጨርሱ ነው ብቃት ማነስ የሚል ታፔላ የተለጠፈላቸው፡፡ ዛሬ እሳቸውም ወንጅሉ ስለተባሉ ይህን ያህል ማለታቸው ይገርማል፡፡ ምነው ትላንትን ረሱት፡፡ ቤንሻንጉል ጉምዝ ብቻ ነው እንዴ አማራውን ያባረረው? ደቡብ ክልልስ? ወያኔ ታሪካዊ ጠላቴ ባለው አማራ ላይ የሚከሰቱ አዲስ ድርጊቶች አይደሉም እኮ እነዚህ፡፡ ይልቅ ባለስልጣኖቹን ከሚያባርሩና ከሚሳደቡ ወያኔ አማራ ላይ ያለውን ጥላቻ  እንዲፍቁ አለቆቻቸው ቢጠይቁ አይሻልም?