Wednesday, August 28, 2013

እኔ በራሴ ላይ የደረሰውን እና ባይኔ ያየሁትን ነው የማወራችሁ!!!

እኛስ ፍፁሞች ነን ......???

እኔ በራሴ ላይ የደረሰውን እና ባይኔ ያየሁትን ነው  ማወራች!!!
ከሚጡ ናሆም

   ከባህር ሲመጡ የሚፈጸምባቸውን ግፍ ብቻ ሳይሆን እዚህ ሀገር በየሰው ቤት ተቀጥረው የሚሰሩትን ሁኔታም መከታተል ማነጋገር ጀመርኩ፡፡ ቀስ በቀስ ግን የተለያ የሚፈጽሙትን ታሪኮች እንደጀብዱ በየቡናው ላይ በየጫቱ..በየድግሱ ቦታ የሚያወሩትን ስሰማ ይገርመኝ ጀመር፡፡ ግርምቴን በግርምት ማህደር አድርጌ መረጃ ማስባሰቤን ቀጠልኩ፡፡ ወርቅ ሰርቀሻል ብለው አሲዘዋት የነበረች ልጅ ከእስር ቤት ስትወጣ ሁለት እስር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዊያ ሴት ለሴት እስር ቤት ውስጥ ሲያደደርጉ እንዳየቻቸው ነገረችኝ፡፡ አናግራቸው ብላ ስማችውንም ሰጠችኝ፡፡   ምን ብዬ ላናግራቸህው..እነዛ የተባሉ ልጆችም ወጥተው የባሰ ሌላውን ሲያሰድቡ አይቻለሁ፣ ሰምቻለሁ፡፡ ብዙ አሳዛኝ ድርጊት የሚያደርጉ አጋጥመውኛል፡፡ ዛሬ ደግሞ የሚጡ ምስክርነት ደስ ብሎኝ እኔም ዳግም ላሰፍረው ወደድኩ፡፡ መልካም ንባብ…..

ተናድጃለ  የምር  በቃ!...ብሽቅ አልኩና ብሽቀቴን መናገር ወድኩ ....
ብቻዬን ምን ቦጣኝ፡፡ ሚያባሽቀኝ አልያም ብሽቅ የሚሆንብኝ አላጣ!!!
ግን ግን ያበሸቀኝ ምን ደሆን ታውቃላች!
እኛ አረብ ሀገር ያለን ሴቶች ዲታዘንልን መፈለጋችን እኛ እየሰራን ያለነው ምን ደሆነ ማየት ሳንችል ግፍ እየተሰራብን መሆኑን ብቻ መደስኮር!!!.. አያናድድም?

   ደሞ ደሞ ለምን በጅምላ ደምናገር ታውቃላቸ ስም ሲጠፋ አንድ ላይ ስለሆነ በስመ በሻ ባንዳይን አይደል የምንታይ አገራችን ውስጥም ቢሆን "አረብ ሀገር የቀመሰች ሴት .... "ይባል የለ? ያቺ ከገጠሪቱ ኢትዮጲያ የመጣችው እና ከመሃል  . የመጣችው እዚህ እኩል ናቸው (ኧረ..እንዲያውም የገጠሪቷ ፈጣን ናት)
 ...በሳውዲ ሪያድ ከተማ ውስጥ ልዮ ስሙን ለይቼ በማላውቀው አካባቢ ነው ምሰራው ኮትራት ሰራተኛ ነኝ 2 አመት ከመጣሁ 6 ወር 15 ቀናት ሆኖኛል፡፡ ታዲያ አረብኛውን ባላቀላጠፈውም እናገራለሁ አንዴት ለሚለው ....... ስለራሴ ሳወራ ላሰለቻችሁ ነው "ወደ ገደለ ወረ " ይባል የለ ....
ሰሞኑን ካሰሪዬ ጋር እህትዋ ቤት ሄድን የት እንደው ባላቅም እራት ግብዣ ተጠርተው አብረው ለመሔድ ነው እዛ ስደርስ 8: 30PM ነበር ስንገባ ሀበሻ አየሁ በጣም ደሳለኝ ካሰሪዬጋ ብዙም ስለማናወራ እህትዋ ቤት በሻ እንዳለች አላውቅም ነበር፡፡ ተቃቅፈን ላየን የተነፋፈቁ ዘመዳሞች እንመስላለን፡፡ እስኪለባብሱ ባገኘነው አጋጣሚ እናወራለን የሷ ሴትዮ ሆስፒታል ነው ምትሰራው፡ ከግብዣው በኃላ በዛው ስራ ትገባለች፡፡ ለዛ ይዛት አትሄድም ልንወጣ ስንል "እዚህ ተቆይኛለሽ"አለችኝ ልጆቿ አያታቸው ቤት ናቸው ሚያስቸግራት የለም፡፡  ካፍዋ ቀምቼ ነበር "አዎ " ያልኩት ግልግል ሔዱ፡፡ እንደ ልብ ሊወራ፣ ሊሳቅ.. ምኑ ቅጡ የብዙ አመት ጓደኛሞች መስለናል፡፡  ምናወራው አናጣም የስዋ አሰሪ 1 ሴት ልጅ ነች ያለቻት አብራቸው ሔዳለች ሰውየው?
እኔጃ አልጠየዃትም ....
ከመጣች አመት 8 ወር እንደሆናት ሌላም ብዙ ነገር ስናወራ አመሸን፡፡ ሰአቱ 2:05 PM ሲል የኔ ሴትዮ ደወለች፡፡
 "ደክሞኛል ነገ ወስድሻለውእዛው እደሪ " ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡ የዚህ ቤት ልጅ ደሞ እኛ ጋር ልታድር ...
እራት በልተን ስለነበር መኝታችንን ማነጣጠፍ ጀመርን ክፍልዋ አነስተኛ ነች አልጋ እና አነስተኛ የልብስ ቁም ሳጥን አለ የሆነ ፍራሽ ይዛ መታ መሬት አነጠፈች፡፡ እኔ ፍራሹ ላይ ልተኛ ብልም እቢ አለች አልጋዋን ለቀቀችልኝ አመስግኜ ተኛው መብራት ጠፋ ........
አዲስ ቤት ስለሆነ ነው መሰል እቅልፍ እቢ አለኝ እሷማ ኩርፋተዋ መሰማት ጀመረ፡፡ ድካም አይደል ስልኬን ይዤ እቅልፌን ጠብቃለሁ ...ኮቴ ሰማሁ ካለሁበት ክፍል ብዙም ያልራቀ "ማን ሊሆን ይችላል "ሴትየዋ መታ ...... አኔጃ ...... እየቀረበ መጣ በሩ አልተቆለፈም ሁሌም አይቆለፍም ብላኛለች፡፡ ቁልፉስ? ..... እኔጃ ......ስልኬን አስቀመጥኩ እና ተሸፍኜ አጮልቄ መጠበቅ ጀመርኩ  ተከፈተ በቀስታ ነበር....... .የሆነ ሰው ገባ ተንቀጠቀጥኩ፡፡ በላይ በላዩ  መተንፈስ ጀመርኩ እንዲህ አይነት ፍራት ፈርቼም አላውቅ፡፡ በሩ ተዘጋ "ማርያምዬ የዛሬን አውጭኝ" ገብርኤልዬ .....ሚካኤልዬ ......ለመኩ .... በዛች ቅስፈት ያላልኩት አልነበረም፡፡ ....... ክፍሉ ጨለማ ነው ለኔ በደንብ ይታየኝ ነበር ጨለማ ውስጥ ስለቆየው ለሱ ግን ብዙም ሚታየው አል መሰለኝም፡፡ ተወላክፎ አልጋው ላይ .........አለ እዛው ኩርምት አልኩ እሱ ምንም አልመሰለው፡፡ ...... እሷም ምንም አትል አልሰማች ይሆን ...... እኔጃ ...... ዝምታ እጁን እላዬ ላይ ጣል አረገው እና አልጋው ላይ ለመውጣት ..... አለ ይሔኔ ያለ የሌለ ሀይሌን ተጠቅሜ ድፍረት ፣ወኔ ፣ቁጭት አግዘውኝ ካልጋው ወረድኩ ስልኬን ይዣለው "ምን ልትሆን ነው ማነህ " ብዬ ጮሁኩኝ መብራቱ የቱጋ እደነበር ጠፍቶብኛል " ምንድን ነው " ብላ እሷ ተነስታ አበራችው የወንድነት መገለጫ አለሁ ብሏል፡፡ ሲያየኝ ግራገባው "ማነች "ብሎ ጠየቀ፡፡ የት እንደምሰራ ነገረችው ..... ምንም ፍርሃት አይታይበትም አልተደናገጠም " አይዞሽ ብር ሰጥሻለው ሀቢብቲ "ብሎኝ እርፍ ደሜ ፈላ፡፡ "ማትወጣ ከሆነ ደውላለሁ ብዬ ስልኬን አሳየሁት ..... ብስጭት ብሎ የሷን እጅ እየጎተተ ይዟት ሔደ፡፡ አለምንም ተቃውሞ ሔደች .......ተናደድኩ አለቀስኩ ምነው አብሬ ሔጄ በነበር !!!!
ቆይታ መጣች አስጠላችኝ ......አይኔን ማየት አፈረች .....
"
በወር ከደሞዜ ያላነሰ ገንዘብ ይሰጠኛል አስገድዶኝ ሳይሆን ከጥቅሜ ብዬ ነው " አለችኝ ምን አገባኝ ዝም እግሬ ላይ ወድቃ "አትናገሪ" አለች ምንስ ቢሆን እንዴት ልናገር ችላለሁ .......ነጋ እኔም ወደቤቴ  ተመለስኩ ግን አሁን በሆነ አጋጣሚ ሴትዮዋ ደርሳባት አናትዋን ብላ ብትገላት ወይም ሌላ ጉዳት ብታደርስባት ተበደልን አይደል ሚባለው የኛ መዝረክረክስ ከምን ይቆጠራል????,