Tuesday, August 27, 2013

ዛሬም የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ፈተና

ዛሬም የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ፈተና…
የዲግሪ ምሩቁ ስቃይ
   በግሩም ተ/ሀይማኖት
ነሀሴ 20 ቀን 2005 ጠዋት ላይ ነው፡፡ ያለሁበት ሱቅ በር ላይ ቁመታም ጠይም ሀበሻ መጥቶ ቆመ፡፡ ምንም መናገር የፈለገ አልመሰለኝም፡፡ ዝም በዝምታ እቃ ሊገዛ ስሎኝ ምን ፈለክ አልኩት፡፡ ምግብ እንደሚፈልግ በእጅ ምልክት ነገረኝ፡፡ መናገር የማይችል መስሎኝ ግራ ተጋባሁ፡፡ እንዴት እኔ ጋር ልትመጣ ቻልክ? ስለው ሳልፍ ሱቁ በር ላይ የተቀባውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ስንደቅ አላማ ሳይ ሀበሻ ናቸው ብዬ መጣሁ አለ፡፡ አጠገቤ ካለ የየመናዊያን ምግብ ቤት አምጥቼ ሰጠሁት፡፡ይስሀቅ መብራቱ ይባላል የመቀሌ ልጅ ነው፡፡በልቶ ሲጨርስ አዲስ ነህ? በየት መጣህ? ስንት ጊዜ..ሆነህ?…የሚሉ ጥያቄዎችን ደረደርኩለት፡፡ ሲነግረኝ ጅማ ዩንቨርስቲ በቢሮ አስተዳደር (በኦፊስ ማንጅመንት) ባችለር ዲግሪውን አግኝቷል፡፡ አዲስ አበባም ሆነ መቀሌ ለእሱ የስራ በራቸውን ሊከፍቱ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሳዑዲ አረቢያ የሚመላለስ ልጅ እዛ ስራ ብትሞክርስ አብረን እንሂድ ይለዋል፡፡ ስራ ካልተገኘስ ብሎ ስጋት ስላደረበት ዘመዱ ቀድሞ ሄዶ ስራ ካገኘ እንዲጠራው ይነጋገራሉ፡፡ በተነጋገሩት መሰረት ልጁም ቀድሞ ይሄድና ሳዑዲያ ውስጥ አንድ ድርጅት ያለው የሚያውቀው መጠጥ ይገዛው የነበረ ደንበኛውን ወንድሜ ተምሮ ተመርቆ ስራ አጣ ይለዋል፡፡
    ‹‹ይምጣ ኢንሽ አላህ ስራ እናስገባዋለን…›› ይለዋል፡፡ ደውሎ ና ስራ ተገኝቷል ይለዋል፡፡ ትንሽ ገንዘብም ልኮለታል እሱም ፈላልጎ ሳንቲም ጨምሮ በጅቡቲ ይመጣል፡፡ ‹‹..ችግር የገጠመኝ ከድሬደዋ ነው…›› ሲል አጫወተኝ፡፡ ድሬ ደሞ ምን አጋጠመህ አልኩት፡፡ የሆነች ልጅ አይቶ እንደወደዳት…እሷን ለማናገር ሶስት ቀን ሁሉ አድሮ ጉዞውን ሊያስተጓጉል ፈልጎ ነበር፡፡ ግን የስራውን መግኘት ሁኔታ አስቦ ልቡን ድሬ ላይ ጥሎ ወደ የመን ነጎደ፡፡ እንደሌሎቹ ሁሉ ከባህር ሲወርድ በአጋቾቹ ተያዘ፡፡ ስልክ ቁጥር አምጣና ደውለህ የሳዑዲያ 1500 ሪያል አስልክ ተባለ፡፡ ቁጥር የለኝም በማለቱ ያየውን ስቃይ ሲነግረኝ በጣም የከፋ እና አሳዛኝ ነበር፡፡ እንዴት ላሳይህ ሰውነቴ ላይ በሙሉ በሲጋራ እያጠሉኝ 13 ቦታ ጠባሳ በጠባሰ ሆኛለሁ፡፡በዛ መቼ በቃ ብለህ ነው፡፡ አንገቴ ውስጥ ገመድ ከተው አንጠለጠሉኝ፡፡ ሁለቴ አንጠልጥለው አወረዱኝ፡፡ ልሞት ብዬ አጣጥሬ ነቃሁ፡፡ እጄን በገመድ አድርገው መኪና ላይ አስረው መሬት ለመሬት ጎተቱኝ፡፡ እጄን ሰበሩኝ፡፡ የያዝኩትን ብር መጀመሪያ ሲፈትሹኝ ወስደውበኛል፡፡ ዱላው ሲበዛብኝ ይልክልኘል ያልኩት ሳዑዲ አረቢያ የለው ልጅ ደውዬ ነበር፡፡ አንዴ አንስቶ አወራኝ እና በኋላ ስልኩን ከነአካቴው አላነሳም አለኝ፡፡ ደበደቡኝ..ደበደቡኝ፡፡ እይ…(የተሰበረ እጁን ገልጾ አሳየኝ፡፡)
   በሲጋራ 13 ቦታ እንዴት እንዳቃጠሉት ጠየኩት፡፡ ብልቱ ላይ፣ መቀመጫው ላይ ደረቱ እና ሆዱ ላይ እንዳቃጠሉት ነገረኝ፡፡ አሁን ምን ታስባለህ ወደ ሀገር መመለስ ወይስ ሳዑዲ ትሄዳለህ ስለው ‹‹..ኧረ.! ሀገሬ ነው የምፈልገው..›› ሲናገር እያንገፈገፈው ነው፡፡ታዲያ ወደ ሀገር መመለስ ከፈለክ ሀረድ IOM ካምፕ ለምን አልገባህም? አልኩት፡፡ እውነትም ሀገር ለመግባት ከሰነዓ ከተማ ከመሞከር ይለቅ ካምፑ ይቀላል ብዬ ነው፡፡እዛም ችግር እንዳለ እና ቶሎ እንደማይመልሷቸው አውቃለሁ፡፡
   ‹‹መጀመሪያማ እዛ ነው የገባሁት፡፡ ግን ከእኔ በፊት የገቡ በጣም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አሉ፡፡ ሶስት አመት የተቀመጡ አሉ፡፡ እዛም አድሜ መፍጀት ነው የሆነብኝ፡፡ እዚህ ያለውን አማራጭ መሞከር ፈልጌ ከመጣሁ ሶስት ቀኔ ነው፡፡..›› አለኝ፡፡ ካምፕ ውስጥ ብልቱ የተቆረጠ ልጅ ነበር ብለውኛል አንዱም ራሱን አጠፋ ብለውኛል አይተሀቸዋል? አልኩት፡፡ ካምፕ ውስጥ ብቻ አይደለም ያየኋቸው ስንያዝም አብረን ነበርን፡፡ ሲቆረጡም አይቻለሁ፡፡…የምናገረው ጠፋኝ፡፡ አፌን ደም ደም አለኝ፡፡ በሰፊው ላውራው ፈለኩ፡፡ ሻይ እንጠጣ አልኩትና የምሄድበትን አስተጓጉዬ ወደ ቤተክርስቲያኑ መታጠፊያ ላይ ያለ ቁርስ ቤት ተቀመጥን፡፡ ላወራ የፈለኩት ሁሉ ጠፋብኝ፡፡ እንደምንም ብዬ እስኪ ስለሁኔታው ንገረኝ አልኩት፡፡ የታሪኩን ፍሰት ሳልስት ለመያዝ በንቃት እየጠበኩት፡፡
    ‹‹ነገሩ ሰቅጣጭ ነው፡፡ በሁለት ጀልባ የተጫነው 80 አካባቢ እንሆን ሆናል፡፡ ከበዛ 90 ብንሆን ነው፡፡ገና መሬት ከመርገጣችን ወዲህ ኑ..እያሉ አዋክበው መኪና ላይ ጫኑን፡፡ የሆነ ጊቢ ውስጥ አጎሩን፡፡ ፍተሻ ጀመሩ፡፡ ብር ብቻ አይደለም የሚፈትሹት፡፡ ሳዑዲ ማን ነው የሚቀበላችሁ? ስልክ ቁጥሩን አምጡ..እያሉ ቁም ስቅል አሳጡን፡፡ እኔ ስልክ ቁጥር ጽፌበት የነበረውን ብጫቂ ረቀት አኘክ አኘክ አድርጌ ጆሮዬ ውስጥ ተፍኩት፡፡ ሲፍትሹ ያገኙትን ገንዘብ ወሰዱብኝ፡፡ ድብደባው ተጀመረ ልብሳችሁን እያወለቃችሁ ለየብቻ መሬት ላይ አስቀምጡ ተባልን፡፡ የሚገርመው ነገር ይህን አይነት ነገር የሚሰሩት ኢትዮጵያዊያ ናቸው፡፡ ብጫቂ ወረቀት ይሰጡህና ስምህን ጽፈህ ያወለከው ልብስ ላይ ታደርጋለህ፡፡ አንድ ክፍል ውስጥ ራቁትህን ትገባለህ፡፡ አስብ ያሳፍራል ሴቱም ወንዱም ፓንት እንኳን ሳታደርግ አንድ ክፍል ውስጥ መለመላህን መታጎር፡፡
   ‹‹..ፈትሸው ሲጨርሱ ወጡ ተባልን፡፡ ከያዛት ብጫቂ ወረቀት ላይ ‹ፋኖስ› ብሎ ተጣራ፡፡ ኢትዮጵያ ነው የሚጣራው፡፡አንዲት ከ16 ዓመት የማትበልጥ ልጅ ራቁትዋን ብድግ አለች፡፡ሰውነቷ በፍርሃት ይንቀጠቀጣል፡፡ በሁለት እጆችዋ ሀፍረቷን ሸፍና ጭንና ጭንዋን እያፋተገች ወደ እሱ ሄደች፡፡ ‹ነይ ወደዚህ አንቺ ብልጥ ሆነሽ ልታታልይን ነው? ስልክ ቁጥሩን በየቦታው ደብቀሽ የጻፍሽው? ብሎ ከየልብሷ ላይ የሰበሰበውን ቁጥር አገጣጥሚ እና ደውይ..› ብሎ ወረቀቱን ሰጣት፡፡በሁለት እጇ ሸፍና የነበረውን ሀፈረቷን እንዴት ለቃ ትቀበለው እፍረትም ይዟታል፡፡ ለቃ እንዳትቀበለው…ብቻ በጥፊ ሲያጎናት ድንጋጤው ነው መሰለኝ ለቀቀችና በአንድ እጇ ወረቀቱን በአንድ እጇ ሞባይል ስልኩን ተቀበለችው፡፡ ያኔ ነጻ አገኛት በታጡ ነካካት፡፡ ዋይ ብላ እሱን ለማስተው ወደኋላ ስታፈገፍግ ›..ዝም ብለሽ ደውይ ብሎ በጥፊ መታት፡፡ ብልቷ አካባቢ እያቆጠቆጠ ያለውን ፀጉር በያዘው ሲጋራ አቃጠለው፡፡ በዚህን ሰዓት ‹.አአአ!…› ብላ ወደ ላይ ስትዘል የያዘችውን ሞባይል ለቀቀችው፡፡ አረቦቹ ደስ ብሏቸው በትዕይንቱ ይስቃሉ፡፡ ይሄ ሙክታር ዪባል የጅማ ልጅ ግን ልጅቷን በዱላ አላስተረፋትም፡፡ በጠረባ ጣላትና ጣቱን እንትኗ ውስጥ ለመክተት ሲታገል አንዱ አላስችል አለውና ‹ምነው አንተ ከሰውም አልተፈጠርክ ሴት ልጅ ያውም ያገርህን ልጅ እንዴት እንዲህ ተደርጋለህ?..ነውር ነው፡፡..› ይለዋል፡፡    
   በቀጥታ ቁጭ ብለው ከሚስቁት የትዕይንቱ ታዳሚዎች የመናዊያን ቀጣሪዎች ወገባቸው ላይ ከሚታጠቁት ስለት ነገር (ጃንቢያ ይባላል) ተቀብሎ መጥቶ ና ወደዚህ ብሎ ጠራው፡፡ ፈራን ሁላችንም ፈራን፡፡ እነዚህ ሰዎች ደም የለመዱ ደም የጠማቸው ናቸው፡፡ ምንም አማራጭ ስለሌለው እሱም ሀፍረቱን በእጆቹ ሸፍኖ ተጠጋው፡፡ አዘንክላት? እዚሁ እያየንህ አርጋት(ተገናኛት) አለው፡፡ፈጽሞ አላደርገውም ከፈለክ ግደለኝ፡፡ ወገኔ ናት እኮ አለው፡፡ ናጥ ያደርገው የነበረውን ስሜት ስታይ የማናዊያኖቹ ክላሽ ስለያዙ ባይፈራቸው የያዘውን ስለት ነጥቆ አሩን የሚያበላው ይመስል ነበር፡፡ በእርግጥም ተናነቁ..የመናዊው ተነስቶ ክላሽ ደቀነበት፡፡ በዚህን ጊዜ እጁን ወደላይ አለ፡፡ ሙክታር ተብዬው የልጁን ብልት በእጁ ይዞ ‹እኔ ላይ ወንድ ልትሆን አይደል ወንድነትህን እንዳውቅልህ ካላደረካት እቆርጥልሀለሁ› አለው፡፡
   ‹‹ወንድነቴን ግፍ በመስራት አይደለም የማሳይህ ይሄን የደቀናችሁብኝን መሳሪያ አውርዱትና ላሳይህ፡፡ ያለበለዚያ ቁረጠኝ እንጂ እሷንስ አላደርግም..› አለው፡፡ ጭካኔውን ተወኝ ሙሽልቅ ሲያደርገው ሁላችንም ደነገጥን፡፡ አንደኛው ግን ከመሀላችን አአአአአአ!!!! ብሎ ዛር እንዳለበት አጓራ፡፡ ድምጹን ከፍ አድርጎም ‹..እናንተ አውሬዎች..› እያለ ተሳደበ፡፡ እሱንም ጠርቶ ተገናኛት ያለበለዚያ እቆርጥሀለሁ ሲለው ፈራ፡፡ ልጅቷ መሬትእንደወደቀች በፍርሃት ትንቀጠቀጣለች፡፡ ብልቱን ተቆረጠው ልጅ ይንደፋደፋል፡፡ ይኛውንም ብልቱን ይዞታል፡፡ ቆረጠውም፡፡ በዚህን ጊዜ   ካሳሁን የተባለ የሮቤ ልጅ የሚደፋደፉትን ለመርዳት ሲጠጋቸው በደም ማፍሰስ ደስታ ላይ የነበረው ሙክታርት በጥፊ ብሎት ከእጁ ስለቱን ሊነጥቀው ሲል ያኛው ባለመሳሪያው በሁለት ጥይት ደረቱን ብሎ ደፋው፡፡ ሌላኛው ደንግጦ ይሁን እንጃ ብድግ ሲል እሱንም በጥይት መታው፡፡ ‹..እስኪ ወንድ ናችሁ አስጥሏት ብሎ ያችን አንድ ፍሬ ልጅ ራቁቷን እንደተኛች በጣቱ ይጫወትባት ጀመር፡፡ ምን እናድርግ ዝም አልን፡፡….በኋላ ቅበሩ ብለውን ከጊቢ ውጭ መሳሪያ ደግነው ቆፍረን ቀበርን፡፡ ልጅቷን ግን ከዛ ጊቢ እስክንወጣ እየተፈራረቁ ተጫወቱባት፡፡ ሌሎቹንም ሁሉ ተጫወቱባቸው፡፡››
   ‹‹..ከዛ መዓት ውስጥ አንተ እንዴት ወጣህ?›› አልኩት፡፡
   ‹‹ ይሄውልህ..ሳዑዲ የጠራኝ ዘመዴ ስልኩን ሲዘጋብኝ በድብደባ ልሞት ነበር፡፡ አማራጭ ሳጣ ከ20 ቀን በኋላ ቤተሰብ ጋር ደወልኩ፡፡ ቀጥታ ከኢትዮጵያ አንቀበልም ስላሉ ሳዑዲ ያለ ሰው ተፈለገና የእኔ ቤተሰቦች ገንዘቡን ለእሱ ቤተሰቦች ሰጡ፡፡ እሱ ልዋጩን ከሳዑዲ በሪያል ላከ፡፡ በጨለማ ብልታቸውን ከተቆረጡት ልጆች ጋር አውጥተው ካምፑ አካባቢ ጥለውን ሄዱ፡፡...ካምፕ ከገባን ከ24 ቀን በኋላ ያች ህጻን ልጅ ደብድበዋት ፊቷ ሁሉ አባጦ መጣች፡፡…››የሚነግረኝ ነገር ሁሉ ውስጤን የሀዘን ከል ቢያለብሰውም፡፡ ብቻዬን ምን ማድረግ እችላሁ?

“የኢትዮጵያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች”

“የኢትዮጵያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች”

የልማታዊ ጋዜጠኞች አንዝህላልነት እና የአብርሃ ደስታ እማኝነት
eth women
ባሳለፍነው ሳምንት በሳውዲ አረቢያ ግፍ ተፈጸሞባቸው ወደ ባገር ቤት የሚሸኙ እህቶች የመኖራቸው መረጃ ደረሰኝ። በተለይም በቅርብ እከታተላቸው የነበሩ አህቶች እንግልት በመጠቆም በዚው በፊስ ቡክ የማለዳ ወግ ዳሰሳየ ላይ አንድ መልዕክት አስላልፊ ነበር! መልዕክቱም ለልማታዊ የሃገር ቤት ጋዜጠኞች ሲሆን የመልዕክቱ ፍሬ ሃሳብ “የምንናገረውን ማመን መቀበል አቅቷችሁ እንደ ጠላት ከምታዩን ረቡዕ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ ሂዱና ከፍተኛ ግፍ ተፈጸደሞባቸው ከሳውዲ ተጠርፈው ወደ ባገር የሚገቡትን የኮንትራት ሰራተኞችን ተመልክቱ !” የሚል ነበር።
ንቁ እዝነ ልቦንና ያልታደሉት ልማታዊ ጋዜጠኞች በቦታው ሄደው ከቤሩት የተመለሱትን ሻንጣ የደረደሩ እህቶች በቴሌቪዥኑ መስኮት ብልጭ አድርገው ከማጥፋታቸው ባለፈ ከሳውዲ ያለጫማና የረባ ልብስ ተደብድበውና ተደፍረው የተመለሱትን ግፉአን ሊያሳዩን እንኳ አልፈቀዱም! ጋዜጠኞቻችን አልተሳሳቱም!!! የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ያን ሰሞን “ስደት ይቅር” ምንቴስ ሰፊ ሽፋን በየሚዲያው እየሰጡ፣ የደበቁትን መከራችን እያሳዩ እያሉ ህዝበ አዳም፣ ሃገሬውን ሲያስለቅሱን የከረሙት ወደ ነፍሳቸው ተመልሰዋል ብየ በማሰቤ ስህተቱ የእኔ ግምት ነው!!! ጉዳታችን እዩት ቀሪው እንዲማርበት ፣ ሃላፊዎቻችን ይዩትና ወደ ዘነጉት የዜጎች ጉዳይ ያተኩሩ ዘንድ የተገፊ ግፉአኑን ጉዳይ ተከታትየ መጠቆሜ በአደባባይ ቃል የገቡትን ይፈጽማሉ ብየ በማሰቤ የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ስህተቴ አንድና አንድ ነው!!! የአረብ ሃገሩን የስደት መከራ የሚፈልጉት ለፕሮፖጋንዳ እንጅ ቀሪውን ማስተማርን እንደልሆነ አለማሰቤ ነው ስህተቴ!
በእንዝህላል ልማታዊ ጋዜጠኞቻችን አዝኘም ብቻ ሳይሆን አፍሬ ዝም ማለቴ ግን እውነት ነው! ዛሬ ማለዳ ግን መልካም መረጃም የሚየ ስፈነጥዝ ባይሆንም መረጃው በመሰራጨቱ የተደሰትኩበትን መጣጥፍ ተመለከትኩ። ሮብ ነሓሴ 15, 2005 ዓም ከአረብ ሃገር ወደ ሃገር የገቡትን እህቶች አብርሃ ደስታ አግኝቷ እንዳነጋገራቸው በማህበራዊ ድህረ ገጽ ካስተላለፈው መልዕክት ለመረዳት በመቻሌ ደስ አለኝ! በገዥው የኢህአዴግ መንግስት አስተዳደር ላይ በተለይም ስለ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመቀሌ ሆኖ በሚያሰራጫቸው የሰሉ ሚዛናዊ ሂሶች ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣው አብርሃ ድስታ ግፉአን እህቶቸችን ቦሌ አየር ማረፊያ አግኝቷቸው ያየውን የሰማውን እጥር ምጥን ባለው የለመድነው መረጃ አቀባበል እንካችሁ ብሎናል። የአብርሃ እማኝነት አስደስቶኝ እኔም ለዛሬ ወግ ዳሰሳ አበቃሁት!
ወዳጃችን አብርሃ ደስታ ሆይ!
የአረብ ሃገሩ የብዙሃን የኮንትራት ሰራተኞች አስከፊ ህይዎት ያጫዎቱህ ወደ ሃገር ለመግባት የታደሉት መሆናቸውን አስረግጨ እነግርሃለሁ! ያየሃቸው የታደሉት ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው! የመንግስት ተወካይ አለን ለማለት አልደፍርም! እውነቱ ይህ ነው! አንተም እንኳን ከግፉአኑ ሰምተህ አሰማህን! ይህ የማናችንም ሃላፊነት መሆን ሲገባው እያደረግነው አይደለም! የእህቶቻችን ህይዎት በአረብ ሃገር ምስክርነቱ ይህ ነው! እንዲህ ይኖራል! የእኔን በዚህ ላብቃና እጥር ምጥን ወዳለችው የአብርሃ ደስታን እማኝነት ከዚህ በታች እንድትመለከቱ ስጋብዝ ለአብርሃ ምስጋና በማቅረብ ጭምር ነው! እኔ አበቃሁ ! ቸር ያሰማን! (ፎቶ: Addis Fortune)
ነቢዩ ሲራከ
By Abraha Desta የኢትዮዽያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች
ሮብ ነሓሴ 15, 2005 ዓም ጠዋት ቦሌ ኤርፖርት ነበርኩ። ኢንተርናሽናል ተርሚናሉ ከዓረብ ሀገራት በተመለሱ እንስት ኢትዮዽያውያንAbrha ተጥለቅልቋል። የተከፉና የተረበሹ ይመስላሉ። ከሰዓት በኋላ ወደ መቐለ ለመመለስ ወደ ሀገር ውስጥ ተርሚናል ገባሁ። ከነዚህ ጠዋት ረጅም ሰልፍ ይዘው ያየኋቸው ተመላሾች የተወሰኑ አገኘሁ። ስለ ህይወታቸው፣ ስለሚደርስባቸው እንግልት ወዘተ አጫወቱኝ። በዓረብ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን እንደሰው አይቆጠሩም፤ ብዙ አካላዊና ስነ አእምራዊ ችግር ይደርሳቸዋል። ብዙዎቹ አብደዋል፣ ራሳቸው አጥፍተዋል። ኢትዮዽያውያን በመሆናቸው ራሳቸው ይረግማሉ፤ በመፈጠራቸው ያዝናሉ። የኢትዮዽያ ኤምባሲ ግን ምንድነው የሚሰራው? የዜጎች ደህንነት መጠበቅ’ኮ የመንግስት ሐላፊነት ነው። የኢትዮዽያውያን ስደትና ግፍ ሀገራችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሊመራት ይችላል።
አብርሃ ደስታ

ትዞራለች … ትዞራለች … ሲደክማት ታርፈና አሁንም ትዞራለች!


በአዕምሮ ሁከት የተለከፈችው እህት በጅዳ!
11-e
አንድ ወዳጄ መሃመድያ ተብሎ በሚጠራው የጅዳ ከፍል ከኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህር ቤት አካባቢ ይህችን በፎቶው ላይ የምታዩዋትን እህት አግኝቶ ሊያነጋግራት ቢሞክርም ፈቃደኛ አልነበረችም። ከየት ነው የመጣሽው? ስትባል”ከመቀለ” ከማለት ባለፈ 11ስሟንና የሆነችውን አትናገርም። ብዙ ሊያግባባት ሞክሮ ያልተሳካለት ይህ ወዳጀ ይህች እህት ያደፈና የተቀደደ ጥቁር “አባያ” ለብሳና መናኛ ነጠላ ጫማ የተጫማችው እህት የአዕምሮ ሁከት እንዳለባት የተረዳው ብዙ ለማነጋገር ሞክሮ በሰጠችው አንዳንድ ምላሽ እንደሆነ ገልጾልኛል!
ልጁን ትምህርት ቤት ሊያስመዘግብ በሔደበት አጋጣሚ በጠራራው ሜዳ ስትንከራተት በማየቱና ምንም መርዳት ባለመቻሉ ያዘነው ወዳጄን መረጃ ይዤ የጅዳን ቆንስል ሃላፊዎች ስልክ በመደወል ይህችን እህት በመጠለያው አምጥተው ሌላው ቢቀር ካሉት የአዕምሮ በሽተኞች ጋር ቀላቅለው ከመኪና እና ከመሳሰሉት አደጋዎች አንዳትጋለጥ ይሰበስቧት ዘንድ ለማሳወቅ ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም!
አንድ ሌላ ወዳጄ ከትላንት በስቲያ የዚህችን እህት አሁን ድረስ በአካባቢው መኖርና ዝም ብላ እንደምትዞር ነገረኝና ወዳለችበት አካባቢ ሔጄ በአካል ለማነጋገር ሞክሬ ነበር። በጠራራው ጸሃይ የውሃ ፕላስቲክ ባንድ እጇ፤ በሌላ እጇ ፊስታል አንጠልጥላ እየሳቀች እና እየተኮሳተረች ክው ክው እያለች 13የምትራመደው እህት አገኘኋት። ብዙ ከተከትልኳት በኋላ አረፍ ስትል ጠብቄ አማርኛ ትችያለሸ? አልኳት “ግደፈኒ” አለችኝ ፊቷን ዘወር እያደረገች! ለማግባባትና ለማቅረብ ሞከርኩ ፣ ልታስቀርበኝ አልቻለችም! ብዙ ተከተልኳት! … ትዞራለች … ትዞራለች … ሲደክማት ታርፈና አሁንም ትዞራለች! በቃ! እንዲህ ሆናለች …
ዛሬም እዚያው አካባቢ እየዞረች እንደምትገኝ ወደ ትምህርት ቤት ለጉዳዩ የሔደ ወንድም አግኝቷት በስልክ ገልጾልኛል። ስትንከራተት አይቶ ሊረዳት የፈለገው ይህ ወንድም እሱም ሆነ ያየውን የዚህች እህት አበሳ ያሳያቸው የትምህርት ቤቱ ሴት ኢትዮጵያውያን መምህራን ተከትለው ሊያነጋግሯትና ሊረዷት ቢፈልጉም ፈቃደኛ ባለመሆኗ ምንም ማድረግ እንዳልቻለ እያዘን ካነሳው ፎቶ ጭምር ልኮልኛል! ዛሬም ይህን መረጃ ለማቀበል ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊ ወደ ቆንስል ጀኔራል ዘነበ ከበደ እና ቆንስል ሙንትሃ ስልክ ደውዬ የነበረ ቢሆንም ሊመልሱልኝ ግን አልቻሉም! ይህ በእንዲህ እንዳለ በተፈናቃይ ሰራተኞች ዙሪያ ጥናት ለማድረግ በአምባሳደር ውብሸት የተመራ ቡድን ዛሬም በጅዳ ከቆንስል ሃላፊዎች ጋር በመምከር ላይ መሆኑን ታውቋል።
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ

Tuesday, August 13, 2013

የአፍሪቃ ስደተኞች በኢጣልያዋ አፑልያ

አውሮጳ/ጀርመን

የአፍሪቃ ስደተኞች በኢጣልያዋ አፑልያ

ከማልታና ከግሪክ ቀጥሎ በርካታ አፍሪቃውያን ስደተኞች የሚጎርፉባት አውሮፓዊት ሃገር ኢጣልያ ናት።በአንዳንድ የኢጣልያ ግዛቶች መንግሥት ህገ ወጥ የሚላቸው አፍሪቃውያን ስደተኞች ደግሞ በኢጣልያ ጎስቋላ ህይወት ነው የሚገፉት።
በሺህዎች የሚቆጠሩ መንግሥት ህገ ወጥ የሚላቸው አፍሪቃውያን ስደተኞች በየዓመቱ ኢጣልያ ይገባሉ ። እነዚህ ስደተኞች ሥራ የማግኘት ፣ የተሻለ ህይወት የመምራት ወደ ቤተሰቦቻቸውም ገንዘብ የመላክ ተስፋ ሰንቀው በአስቸጋሪው የባህር ላይ ጉዞ ከሞት አምልጠው በተለያዩ የሃገሪቱ የባህር ጠረፎች በኩል ኢጣልያ ቢደርሱም የሚያልሙትን ሁሉ የማግኘት ዕድላቸው የመነመነ ነው ። ጥገኝነት ያላገኙት ደግሞ በአሰዛን ሁኔታ የወንጀለኛ ቡድኖች ሰለባ ሆነው ይሰቃያሉ ። የዶቼቬለዎቹ አሱምፕታ ላቱስ ና ዩልያ ሃን ጥሩ ተስፋ ሰንቆ ወደ ኢጣልያ የሄደ አንድ በደቡብ ምሥራቅ ኢጣልያው የአፑልያ ግዛት የሚገኝ አፍሪቃዊ ስደተኛ ያለበትን ሁኔታ ተመልክተዋል ። ከካርቶንና ከፕላስቲክ ከተቀለሰው ሊወድቅ ከተቃረበው ደሳሳ ጎጆ ውጭ ዝንቦች ያንዣብባሉ ፤ ሽታው ከሩቅ የሚተነፍገው ሳምንታት ያስቆጠረው ቆሻሻ ተከሞሯል ። በስፍራው ይህን መሰል ብዙ ጎጆዎች ይገኛሉ ። ንጹህ የመጠጥ ውሐ ኤሌክትሪክም ሆነ የመፀዳጃ ቤት የለም ። ነዋሪዎቹ አፑልያ ኢጣልያ ውስጥ የሚገኘውን ይህን አካባቢ የጎስቋሎች መንደር ወይም ጌቶ ነው የሚሉት ።

በአንደኛው ጎጆ ውስጥ አንድ ፍራሽ ላይ 5 ሰዎች ተኝተዋል ። በጥቂት ሴንቲሜትሮች ርቀት የሚገኙ ሌሎች 10 ባዶ ፍራሾችም በዚሁ ጎጆ ውስጥ አሉ ። ከላይ የሚንጠለጠሉ ገመዶች እንደ ልብስ መስቀያ ያገለግላሉ ። ወለሉ ላይ ጫማዎች ተደርድረዋል ። በፕላስቲክ ሳህኖች ምግብ ተቀምጧል ። አትሞ
ጎጆዋ የኢብራ ምባኬ ፋልና በአመዛኙ ከምዕራብ አፍሪቃ የመጡ የሌሎች 20 ስደተኞች መኖሪያ ናት ። ጎጆዋ ጠባብና ብዙ ሰዎች የሚኖርባት በመሆኗ አየር የታፈገና መጥፎ ጠረንም ያለው ነው ። ኢብራ ድህነትን ሸሽቶ ህይወቱን ለሞት አጋልጦ በአደገኛው የባህር ላይ ጉዞ ከሴኔጋል ትልቅ ተስፋ ይዞ ወደ ደቡብ ኢጣልያዋ የባህር ዳርቻ የመጣው የዛሬ 12 ዓመት ነው ።
«እዚህ የመጣሁት የራሴን ህይወት ለማሻሻል የሚረዳኝ ጥሩ ሥራ ማግኘት እችላለሁ ፤ ሴኔጋል የሚገኙትንም ቤተሰቦቼን ለመርዳት የሚያስችለኝ ጥሩ ገንዘብ አገኛለሁ ብዬ ነበር ። »
እስካሁን ግን ኢብራ በኢጣልያ የሚመኘውን ህይወት አላገኘም ። ኑሮ በኢጣልያዋ የባህር ዳርቻ አፑልያ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኖበታል ። የ32 ዓመቱ ኢብራ በአገሩ የኮራ አናፂ ነበር ። ኢጣልያ እንደሄደ በሙያው መሥራት ባይችልም መጀመሪያ ላይ ጣልያኖች መሥራት የማይፈልጉትን ሥራ ማግኘት ችሎ ነበር ። ጥሩ ክፍያ ባያገኝበትም ከእርሻ ቦታ አትክልትና ፍራፍሬ ይለቅም ነበር ። ያኔ ጣሊያኖች ንቀው የማይሰሩት ይህ ሥራ ዛሬ የሰማይ ያህል ርቋል ። አሁን እንደ ቀድሞው በቀላሉ የሚገኝ ሥራ አልሆነም ። በዚህ የተነሳም አሁን የሚሰራው አጥቶ ሥራ ፍለጋ ሲዋትት ነው የሚውለው ። ኢብራን ለዕለት ቀለቡ ብቻ ሳይሆን አገሩ ሴኔጋል ለሚገኙት ዘመዶቹም ነው የሚያስበው ። ሥራ በነበረው ጊዜ ከሚያገኘው ገንዘብ ቆጥቦ ይልክላቸው ነበር ። አሁን ግን ያን ማድረግ አልቻለም ።

«ወደ አገር ቤት ገንዘብ መላክ ካቆምኩ 3 ወር ሆነኝ ። ሥራም ሆነ ገንዘብ እንደሌለኝ ልገልፅላቸው ብሞክርም የሚያምነኝ አላገኘሁም ። እነርሱን ዘንግቼ አውሮፓ የምንፈላሰስ ነው የሚመስላቸው »
ኢብራ ሥራ ከማጣቱ በፊት በሰዓት 3 ዩሮ ለሚከፍሉት ካፖላሪ ለሚባሉት ለኢጣልያና ለአፍሪቃ ማፍያዎች ይሰራ ነበር ። የስራ ውል ወይም ኮንትራት እንዲሰጠው ጠይቆ ስላልተሳካለት አቋርጦታል ። ኢብራ የኮንትራት ሥራ ይዞ ከሥራ ቢባረር እንኳን ከመግሥት ጥቂትም ቢሆን ገንዘብ ሊያገኝ እንደሚችል ያውቃል ። ይሁናና ለኢብራ ስራ የሚያመቻቹት እነዚህ ማፍያዎች ለመብቶቹ ደንታም የላቸውም ። ማፍያዎቹ ኢብራና መሰሎቹ ሊያገኙት ከሚገባው ገንዘብ 50 በመቶውን ወደራሳቸው ኪስ ያስገባሉ ። እነ ኢብራን በአነስተኛ ገንዘብ ቀጥረው የሚያሠሩት የአካባቢው ገበሬዎች ብዙ ያተርፉባቸዋል ። ኑሮ በኢጣልያ ያልተሳካለት ኢብራ አሁን ወደ ሃገሩ ወደ ሴኔጋል መመለስን እንደ ሽንፈት ነው የሚቆጥረው ። ወደ ሃገሩ ለመመለስ ቢወስን እንኳን ቲኬት መግዣ ገንዘብ የለውም ። ለክፉ ቀን ብሎ ያጠራቀመው ገንዘብም ቢሆን ተሟጧል ። አሁን ምናልባት ሥራ የሚሰጥ ባገኝ ብሎ በአትክልት እርሻዎች አካባቢ ይዘዋወራል ። ኑሮው ከቀድሞው አሁን ከብዶታል ። በአካባቢው እርዳታ የሚለግስ ደግሞ አንድ ድርጅት ብቻ ነው ።

« እዚህ ሲመጣ የምናየው ብቸኛው ድርጅት የካቶሊካውያን የበጎ አድራጎት ድርጅት ካሪታስ ነው ። ባለፉት ሁለት ወራት ሶስት ጊዜ ያህል ብቻ ነው የመጣው ። ሩዝ ፓስታ እና ቲማቲም ያከፋፍለናል ።»
በኢጣልያዋ የአፑልያ ግዛት በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ይኖራሉ ። አብዛናዎቹም መንግሥት ህገ ወጥ የሚላቸው ስደተኞች ናቸው ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀው በጎርጎሮሳውያኑ 2013 የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ከጥር እስከ እስካለፈው ሰኔ ወር ድረስ ፣ 8 ሺህ አፍሪቃውያን ስደተኞች ደቡብ ኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ ገብተዋል ። የሚመጡትም በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ውስጥ ሥራ ፍለጋ ነው ። እናም ከቀናቸው አብዛኛዎቹ ኢጣልያ ላይቆዩም ይችላሉ ። ያልሆነላቸው ደግሞ ኮፖራሊ በተባለው የወንጀለኞች ቡድን ስር እዚያው ኢጣልያ ውስጥ በሚገኙት የአትክልት እርሻዎች መስራት ይሆናል ዕጣቸው ። የአካባቢው ነዋሪዎች አፍሪቃውያኑ ስለሚገፉት ጎስቋላ ህይወት ያውቃሉ ። አንዳንዶቹ በአካባቢው አሁን ለነርሱ የሚሆን ስራ አንደሌለ ሲናገሩ ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ስደተኞቹ አመፅ እንዳያስነሱ ስጋት አላቸው ።
« በርካታ አፍሪቃውያን እዚህ እየመጡ ሥራ እንዳለ ይጠይቃሉ ። ሆኖም እዚህ ሥራ የለም ። በአንድ ወቅት ከመካከላቸው አንዱን ቀጥሬው ነበር ። ይሁንና አሁን ለርሱ የሚሆን ሥራ የለኝም ። »
«ወደ ተጎሳቆለው መንደር አልሄድኩም ። ሆኖም በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ሰምቻለሁ ። ሁኔታውንም ካሉበት ችግር ለማምለጥ እንደ አመፅ ማስነሻ አድርገው ሊጠቀሙበትም ይችላሉ ። ይህም መንግሥት ምንም እንደማያደርግ ያሳያል ። »
አስተያየት ሰጭዎቹ ይህን ቢሉም በካፖላሪዎች ወይም በማፍያዎች ጉዳይ ውስጥ ገብተው መናገር ግን ይፈራሉ ። ኢብራ እንደሚለው መንግሥትም ቢሆን ስደተኞቹን ዞር ብሎ አያይም ።
« ባለሥልጣናቱ በምንም ዓይነት መንገድ አይረዱንም ። »
የአፑልዪ ከንቲባ ጅያንፍራንኮ ሳቪኖ በአፑሊያ የሚኖሩትን አፍሪቃውያን ስደተኞች ለመርዳት ምንም አለማድረጋቸውን ያምናሉ ። ምክንያት የሚያደርጉትም ሃገሪቱ አህን ያለባትን ችግር ነው ።
«የኤኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ነው ያለነው ። ያም ማለት እኛም ጎስቋላው መንደር እንደሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ሥራ የሚያሻቸው ብዙ ሰዎች አሉን ። ኢጣልያ ውስጥ ከመንግሥት ተቋማት አንስቶ እስከ አካባቢ ባለሥልጣናት ድረስ እጅግ ከፍተኛ የኤኮኖሚ ችግር አለ ። በዚያ ላይ ደግሞ የስደተኞች ጉዳይም ሌላው ተጨማሪ ችግር ነው ። »
በአሁኑ ጊዜ ከግሪክ ቀጥሎ አውሮፓውያንን የሚያስጨንቀው የኢጣልያ ችግር ሆኗል ። ሃገሪቱ ከገጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ ሌላ በየጊዜው በስደተኞች መጥለቅለቋ አሳሳቢ ነው ። አርካንጄሎ ስደተኞችን በተቻላቸው መጠን የሚረዱ የካቶሊክ ቄስ ናቸው ።
አፍሪቃውያኑን በየጊዜው ይጎበኟቸዋል ። ጣሊያንኛ እንዲማሩ የቋንቋ ኮርሶችን በማዘጋጀት እንዲሁም በተቻለ ሁሉ ስደተኞቹን ለማፅናናት ይሞክራሉ ። በእርሳቸው አስተያየት መንግሥት ስደተኞችን ላለመርዳት ችግሩን ሰበብ አድርጎ ማቅረቡ ተቀባይነት የለውም
«የኢጣልያ ተቋማት የሆኑት የፖሊስ ና የኢሚግሬሽን ቢሮዎች ማከናወን የሚገባቸውን እየሰሩ አይደለም ። ከዚህ ችግር በስተጀርባ ያሉት እነርሱ ናቸው ። ሁኔታው እንዲቀጥል ይፈልጋሉ ብዮም አስባለሁ ። ያ ካልሆነ ግን ባለቸው ሥልጣንና በስራቸው ያለውን አማራጭ ሁሉ ተጠቅመው ችግሩን ለምን አያስወግዱም ? »
ይሁንና ቄስ አርካንጄሎ ከኢጣልያ ቢሮክራሲ ጋር የተያያዘውን ይህን ችግር የመፍታት አቅም እንደሌላቸው ነው የሚያስረዱት ። አሁን ለኢብራ በአውሮፓ የተሻለ ህይወት የመምራት ተስፋው ወደ ቅዠት ተለውጧል ። አሁን ያለው አማራጭ አዲሱ መኖሪያው በሆነው በጎስቋላው መንደር እየኖረ ሥራ ፍለጋውን መቀጠል ብቻ ነው ።
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ

Saturday, July 6, 2013

ንጉስ አብርሃ በየመን እንዴት ነገሰ (ክፍል 2)


       
                      በግሩም ተ/ሀይማኖት
    ንጉስ አብርሃ የየመን ንጉስ ነበር፡፡ እንዴት? የንጉስ አብርሃን በየመን መንገስ በተመለከተ ለማስጨበጥ የፈለኩትን ሀሳብ ጥሩ መወያያ ያደረጉት ወዳጆቼ ሰፋ አድርጌ እንድጽፍ አድርገውኛል፡፡ ችርስ!!! እንሱንም ከመወያይት አያርቃቸው፡፡ ታዲያ ተወያይቶ ምግባባትን እንጂ ግራ መጋባትን እንዳያድለን እየለመንኩ ነው፡፡ እስካሁን ላለው በመግባባት መሆኑ ያስደስተኛል፡፡ በተለይ ወዳጄ ፍሬሰናይ ከበደን፣ ፍጹም ዘሚካኤልን ዳኒን ሳላመሰግን አላልፍም፡፡ ታሪኩ ሊነበብ የሚገባው ነገር ቢሆንም ቀልድ በዛበት። ያልከ/ሽ/ኝ ፍጹም ዘሚካኤል እቀበላለሁ፡፡ ግን ለመዝናኛነትም አስቤ ነው፡፡ አንተን ብሎ አዝናኝ እረፍ ካላችሁም ምን አደርጋለሁ፡፡ ‹‹…አላለልኝም እችለዋለሁ…›› የሚለውን እያቀነቀንኩ በልሙጡ አስነካዋለሁ፡፡ ደግሞ እኮ ንባብ ቶሎ የሚሰለቻቸው ብዙ መኖራቸውን ከግምት በመክተት ነው፡፡ ግን በራሴ ጽሁፍ…

    በመቀጠል.. በመጀመሪያ ታሪኩ ትክክል አይመስለኝም። ምክንያቱም በወቅቱ የነበሩት ንጉስ አፄ ካሌብ ናቸው አብርሃ ደግሞ የጦር አበጋዝ ነው። (ምክትል እንጂ ዋና አይደለም) ወይም መከላከያ ሚኒቴር ነው። የእሱ ምክትል ደግሞ ታናሸ ወንድሙ አፅብሃ ይባላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጀመሪያ የመንን የያዘው (የተቆቆጣጠረው) አብርሃ ሳይሆን አፅብሃ ነው። (ፈጽሞ ስህተት) ለዚህ ማስረጃ ብትጠይቁኝ ላቀርብላችሁ እችላለሁ…የአብርሃንም ሆነ የአፅብሃን እንዴት እንደሞቱ ልነግርህ እችላለሁ…. በማለት ያሰፈርከው ወዳጄ ዳኒ በጣም ስህተት መሆኑን በቀይ ስክርቢቶ ሳይሆን  ጎላ ባለ ቀይ ፓርከር ኤክስ አድርጌ ያለህን ማስረጃ እንድታቀርብ እጋብዝሀለሁ፡፡ በወቅቱ የነበሩት ንጉስ ካሌብ መሆናቸውን እኔም ገልጫለሁ፡፡ አብርሃ ወ አጽብሃ ከዚህ ጋር የተገኛኘ ነገር የላቸውም፡፡ አብርሃ ወ አጽብሃ እኮ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሆነው እንጂ የየመን ንጉስ ሆነው አያቁም፡፡ አረ ሼም ነው ሰዎቹን ያለ ቪዛ ያለ ይለፍ ወረቀት ከሀገር አወጣሀቸው እኮ፡፡ ሁለቱም ወንድማቾች  ውቅሮ ከሚባለው በቅርብ ርቀት ነው የመቃብር ስፍራቸው፡፡ (ባለራዕዩ መሪያችን ቢኖሩ የአብርሃ ወ አጽብሃ ታሪክ ወይም መቃብር ለትግራይ እንጂ ለቀሪው ኢትዮጵያ ህዝብ ምኑ ነው? ይሉን ነበር እንደ አክሱም ሀውልት፡፡ ነፍስ ይማር)
 
      በፊት እንደገለጽኩት አብርሃ አሪየልን ገሎ በመንገሱ የኢትዮጵያው ንጉስ አፄ ካልብ ተናደዱ፡፡ በመናደዳቸውም አብርሃን ለመውጋት ምለው ነበር፡፡ አብርሃ በብልጠቱ ማህላቸውን ካስነሳቸው በኋላ አምኖ ሊቀመጥ ባለመቻሉ የሚያስደስታች ነገር ለመስራት ብዙ ይጥር ነበር፡፡ ሰዎች ከየመንም ተነስተው ሆነ ከሌላ ቦታ የመንን አቋርጠው ወደ ካባ (መካ) ሲሄዱ ያያል፣ ይሰማል፡፡ አሁን ባብ አል-የመን የሚባለው አካባቢ በጣም ግዙፍ ቤተክርስቲያን ለመስራት አሰበ፡፡ ያሰበውን ቂም ይዞብኛል ብሎ ለፈራው አፄ ካልብ ‹‹…እነሆ በረከት ንጉስ ሆይ የሚያስደስትህ ከሆነ ይህን ልስራ..›› አለ፡፡ ፍቃድም አገኘ፡፡ ረጅም ጊዜ የወሰደ "አል ቊለይስ" የተባለ ቤተክርስቲያን ሰራ። በአይነቱም ሆነ በግዝፈቱ በዛን ወቅት በጣም የተለየ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ይህ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ለጉብኝት ክፍትሆኖ አለ፡፡

   አዋጅ አስነገረ፡፡ ‹‹..እዚሁ በቅርቡ ትልቅ ቤተክርስቲያን እንደ መካ ያለ ስለሰራን መካ በመሄድ ፋንታ እዚህ ተጠቀሙ፡፡ ይህ ማለት እምነታሁን ለውጡ ማለት አይደለም፡፡ ሁሉም በእየእምነቱ አለ፡፡ ከመካ የመጣ ሰው ወደዚህ ቤተክርስቲያን በመግባት ቤተክርስቲያኑን በሰገራ እና በሽንት አቆሸሸው ይላል የጻፉት ታሪክ፡፡ ሲቀጥልም አብርሃ ይህንን በተመለከተ ጊዜ ንዴቱን መቆጣጠር አልቻለም ነበር። ስለዚህ ሰራዊት አዘጋጅቶ መካን ለመውረርና ለማጥፋት ወሰነ።

   ካዘጋጀው 13 ዝሆኖች መካከል ሙሃሙድ የሚባል ግዙፍ ዝሆን ይገኝበታል። (The year of elephant ተብሎ ያ-ወቅት የሚጠራው በዚህ ምክንያት ነው) ለጦርነቱ ጉዞ ሰራዊቱን ለማሰባሰብ ‹‹እንቁም›› ያለበት ቦታ ዛሬ ድረስ ‹‹ንቁም›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ታክሲ ገብተህ ንቁም ብትል እዛው ወስደው ያወርዱሀል፡፡ ጉዞው ተከውኖ አብርሃ እያሸነፈ መካ ደረሰ። የነብዩ አያት አብዱል ሙጠሊብ ያቀረቡትን እርቀ ሰላም አልቀበል ብሎ ካባን ለማትፍረስ ጉዞውን ቀጠለ። የነብዩ አያትም ከተማዋ ከሚደርስባት ሰማያዊ መቅሰፍት ይጠበቊ ዘንድ ከከተማ ወጥተው ወደ ከፍታ ቦታ ከነቤተሰቦቻቸው እንዲሸሹ ለሰዎች ነገሩ፡፡ ሽሽቱ ቀጠለ..…

    የአብርሃ ጦር መካ መግቢያ ላይ አልሙሃሲር የተባለ ሸለቆ እንደደረሰ በወፍ መንጋ ተከበበ ተደበደበም። አብርሀም ከዚህ ጥቃት ለመሸሽ ወደ የመን ተመለሰ ዳሩ ግን በመንገድ ሳለ በጥቃቱ ስጋው ተበጣጥሷል። (ይህ ነው ቢባልም ጂዛን ላይ እንደሞተ ነው የሚነገረው፡፡ ያውም ወፏ የያዘችውን አጥንት ስትለቀው ወርዶ በረቀሰው የሚልም አለ፡፡)
 
     አብርሃ በስልጣን ላይ ባለበት ወቅት ያው ለንጉስነቱ እንዲሰግዱለት እንዳስገደዳቸው እነሱም አንሰግድም እንዳሉት ይነገራል፡፡ ታዲያ ብልሁ አብርሃ የቤቶቻቸውን በሮች ከአንድ ሜትር ትንሽ ብቻ ከፍ አድርጎ በማሰራቱ ሲወጡ እና ሲገቡ የግዳችን ሰገዱለት ይባላል፡ ለዚህ ይባላል ግን ማረጋጫ አለው፡፡ አሁን አሮጌው ሰነዓ የሚባለው ባብ አል-የመን ያሉ በእሱ ጊዜ የተሰሩ 14000 ቤቶች ምስክርነት ለመስጠት ቆመዋል፡፡ ቤቶቹን በተመለከተ ዳግም ልመለስበት እስኪ….ሰላም አሰንብቶ ያገናኘን፡፡